በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜሮ


የዓመቱ የዓለም የኤድስ ቀን ሎጎ
የዓመቱ የዓለም የኤድስ ቀን ሎጎ

የዘንድሮው የዓለም የኤድስ ቀን እየታሰበ ያለው “ዜሮ ማግለል፣ ዜሮ በኤችአይቪ መያዝ፣ ዜሮ የኤድስ ሞት” በሚል መርኅ ነው፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:22:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


የ “ዜሮ ራዕይ” ወይም “ዘመቻ ዜሮ” መሪ ሃሣብ በኤችአይቪ አንድም ሰው እንዳይያዝ፣ በኤችአይቪ ምክንያት አንድም ሰው እንዳይገለል፣ በኤድስ ምክንያት አንድም ሰው እንዳይሞት በጋራ መንቀሣቀስ፤ ከኤድስ ነፃ የሆነ ትውልድን ወደመፍጠር መፍጠን ነው፡፡ ይህ የረዥም ጊዜ ዕቅድ አይደለም፡፡ ይህ የመካከለኛ ጊዜም ዕቅድ አይደለም፡፡ ይህ በመጭዎቹ ሃያ አምስት ወራት ውስጥ፣ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር እስከ 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ መጨበጥ ይቻላል ተብሎ የተቀመጠ ግብ ነው፡፡ “ይቻላል?” …

“ዜሮ ማግለል፣ ዜሮ በኤችአይቪ መያዝ፣ ዜሮ የኤድስ ሞት”
“ዜሮ ማግለል፣ ዜሮ በኤችአይቪ መያዝ፣ ዜሮ የኤድስ ሞት”

ዛሬ፤ ኅዳር 22 የዓለም ኤድስ ቀን ነው፡፡ አሁን ባለንባት ሰዓት በዓለም ላይ 34 ሚሊየን ሰው ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ ይገኛል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤድስ መርኃ ግብር - ዩኤንኤድስ መረጃ መሠረት ባለፈው 2011 ዓ.ም ውስጥ በቫይረሱ አዲስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 ሚሊየን 500 ሺህ ነው፡፡

በዚያው በ2011 ዓመት ውስጥ በኤድስ ምክንያት 1 ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ ሰው አልፏል፡፡

“ከጥቂት ዓመታት በፊት የነበረው የኤችአይቪ ፈጣንና የሰፋ መዛመት እየቀነሰ ነው” ሲል ዩኤንኤድስ አበረታችና በጎ ዜናም አብሮ አውጥቷል፡፡

ዘንድሮ በአፍሪካ ከፍተኛው የሥርጭት መጠን ማሳያ ካላቸው ሃገሮች መካከል ስዋዚላንድ ሠንጠረዡን በ26 ከመቶ ስትመራ ቦትስዋናና ሌሶቶ በ23.4 እና በ23.3 ከመቶ ይከተሏታል፡፡ የዛሬ አሥር ዓመት አካባቢ የዓለም የኤድስ ሥርጭት ጣሪያ ሆና ዝርዝሩን ስትመራ የነበረችው ደቡብ አፍሪካ ብዙ ዕድገት አስመዝግባ ዛሬ በ17.3 ከመቶ የሥርጭት መጠን አራተኛ ነች፡፡

የዛሬ የኤችአይቪ ሥርጭት በዓለም ዙሪያ - ምንጭ፡- የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤድስ መርኀግብር
የዛሬ የኤችአይቪ ሥርጭት በዓለም ዙሪያ - ምንጭ፡- የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤድስ መርኀግብር

ዚምባብዌ፣ ናሚቢያ፣ ዛምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ማላዊ እና ዩጋንዳ እንደአሠላለፋቸው ከአምስተኛ እስከ አሥረኛ ሆነዋል፡፡ በተለይ ማላዊ እና ቦትስዋና 72 ከመቶ እና ከዚያም በላይ በሆነ ልዩነት የኤችአይቪን የሥርጭት መጠን መቀነስና መቆጣጠር መቻላቸው ብዙ ሙገሣንና ጭብጨባን ከዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ አትርፎላቸዋል፡፡

ለመሆኑ በአንድ ወቅት ደቡብ አፍሪካንና ሕንድን ተከትላ በዓለም ሦስተኛ የነበረችው “የኤችአይቪ ሥርጭት መናኸሪያይቱ” የኢትዮጵያ የዛሬ ሠልፍ የት ጋ ይሆን? ምላሹስ በምን ሁኔታ እየተካሄደ ነው? የሥጋት አካባቢዎች ይኖሩ ይሆን? አዎን፣ አሉ፡፡ ውይይት ይዘናል፡፡

አቶ ዓለሙ አኖ፣ በኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት የዘርፈ-ብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዋና ዳይሬክተር፤ አቶ ደረጀ ዓለማየሁ፣ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች ማኅበራትና መረቦች መረብ ዋና ዳይሬክተር፤ አቶ መንግሥቱ ዘመነ፣ የአንጋፋውና በኢትዮጵያ ከግዙፎቹ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ሰዎች ማኅበራት አንዱ የሆነው የመቅድም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ዶ/ር አጎናፍር ተካልኝ፣ ለኤችአይቪ/ኤድስ የሚሰጠው ምላሽ ቀዳሚ ተሣታፊ፣ መሪና ተሟጋች፣ እንዲሁም አሁን የኢትዮጵያ የወባ መከላከያና መቆጣጠሪያ ኮንሰርቲየም ዋና ዳይሬክተር በውይይቱ ውስጥ ይሣተፋሉ፡፡

ውይይቱን ያዳምጡ፤ እርስዎም ሃሣብዎን በመስጠት ይሣተፉ፡፡
XS
SM
MD
LG