በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያውያን ድምጽ እና የህዝብ ተወካዮች በአሜሪካ


አቶ አንድነት እምሩ ከኢትዮጵያውያን ድምጽ አንድነት (የመራጮች ድምጽ)
አቶ አንድነት እምሩ ከኢትዮጵያውያን ድምጽ አንድነት (የመራጮች ድምጽ)

የኢትዮጵያውያን ድምጽ አንድነት የቮተር ቮይስን ቴክኖሎጂ ስለሚጠቀም፣ በተለምዶ መጠሪያው “ቮተር ቮይስ፣ ወይም የመራጮች ድምጽ” ይባላል፡፡ የተቋቋመው እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወይም ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ነው፡፡ መራጮች ድምጽ ማሰማት ያለባቸው፣ በምርጫ ወቅት ብቻ ሳይሆን፣ ከምርጫም በኋላ የመረጧቸው ተወካዮቻቸው እንዲሰሟቸው ድምጻቸውን ያለማቋረጥ ማሰማት እንዳለባቸው የቮተር ቮይስ መስራቾች ይናገራሉ፡፡

ዋነኛ ዓለማቸው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳዮች እየተከታተሉ በተለይም ከዩናይትድ ስቴትስ በኩል የሚደረጉ የፖሊሲ ጫናዎች፣ ግፊቶች ወይም የመረጃ ክፍተቶች ሲፈጠሩ መራጭ የሆኑ ኢትዮጵውያውን ዜጎች ተወካዮቻቸውን በቀጥታ ማግኘት የሚችሉበትን መድረክ ማመቻቸት መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ላለፉት በርካታ ወራት በአባይ ግድብ ዙሪያ ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን አሁን ደግም ሰሞኑን በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክልልና በፌደራሉ መንግስት መካከል በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ፣ “ከ6ሺ 500 በላይ የሆኑ ሰዎችን በማስተባበር ወደ 120ሺ ደብዳቤዎችን” ወደ ተለያዩ አካላት መላካቸውን ገልጸዋል፡፡ የቮተር ቮይስ መስራቾች ከሆኑት መካከል አንዱ የሆኑትን አቶ አንድነት እምሩን የዛሬ የኢትዮጵያውያን በአሜሪካ እንግዳ አድርገናቸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የኢትዮጵያውያን ድምጽ እና የህዝብ ተወካዮች በአሜሪካ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:26 0:00


XS
SM
MD
LG