በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሴቶች በፖለቲካ እንዳይሳተፉ እና ለአመራርነት እንዳይበቁ የሚያከላክሉ ችግሮች እና አስቻይ መንገዶች 


በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት የሴቶች የፓርቲ ፖለቲካ ተሳትፎ እድገት በማሳየት ላይ እንደኾነ ልዩ ልዩ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡የኢትዮጵያ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤትን እንደ አብነት የወሰደው፣ ዴሞ ፊንላንድ የተባለ ተቋም ጥናት፣ በምክር ቤቱ የሴቶች ተሳትፎ 41 ነጥብ 5 መድረሱን በአስረጅነት ይጠቅሳል፡፡

በርካታ ፈተናዎች ባሉበት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምኅዳር ላይ እየታየ ያለው የሴቶች የፓርቲ ፖለቲካ ሱታፌ ግን፣ ከጾታዊ ማንነታቸው እና ከእናትነት ሓላፊነታቸው ጋራ እየተያያዙ በሚሰነዘሩ እይታዎች እና አቋሞች፣ የእድገቱን ቀጣይነት የሚያከላክሉ ችግሮች እና ተግዳሮቶች እንዳሉበት ይስተዋላል፡፡

ሴቶች ከጥንቱም ወደ ፖለቲካ እንዳይገቡ ከማከላከል ጀምሮ፣ ከገቡም በኋላ በጨቅላ ልጆቻቸው እያባቡ የሚያስጠነቅቋቸው ቤተ ሰዎቻቸው እና ባልንጀሮቻቸው መኖራቸውን አስተያየታቸውን የሰጡ ሴት ፖለቲከኞች ይናገራሉ፡፡ በፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድም ሴት አባሎቻቸውን ለአመራርነት እንዲበቁ የማበረታታት አሠራር እንደሌለ ይተቻሉ፡፡

ሴቶች በፖለቲካ እንዳይሳተፉና ለአመራርነት እንዳይበቁ፣ የዕውቀት ማነስ እና የመረጃ እጥረት እንደ ምክንያት ቢጠቀሱም፣ "ዕውቀት እያላቸው ወደፊት መምጣት የማይፈልጉ አሉ፤" የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ ፓርቲዎች፥ የመሪነትን ሓላፊነት በመስጠት የሴቶችን ዐቅም ሊያሳዩ እንደሚገባ ይመክራሉ፡፡ የፖለቲካ ንቃታቸውን የሚጨምሩ እና ፍትሐዊ መብታቸውን የሚያስጠበቁ ተቋማትም፣ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ እድገቱን ጠብቆ እንዲቀጠል የማስቻል ሚና እንዳላቸው አስተያየታቸውን የሰጡ፣ ኹለት ሴት ፖለቲከኞች ገልጸዋል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ/

XS
SM
MD
LG