ዋሽንግተን —
አሸናፊ በሕመም ምክንያት በጡረታ እስከተገለለባቸው ያለፉት ጥቂት ወራት በአሜሪካ ድምፅ የአማርኛና የእንግሊዝኛ አገልግሎቶች ለሰላሣ አራት ዓመታት አገልግሏል፡፡
የኬሚስትሪ ምሩቅ የነበረው አሸናፊ አበጀ ወደ ጋዜጠኝነት ሙያ ከገባ በኋላ በፈጣን ሁኔታ ከሙያው ጋር መዋሃድና በአድማጮችም ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን የበቃ የራዲዮ ጋዜጠኛ ሆኗል፡፡
አሽናፊ አቅዶ የሚሠራ፣ የጋዜጠኝነትን ሥነ ምግባር አክባሪና ታታሪ እንደነበር አብረውት ላለፉት ዓመታት የሠሩ ባልደረቦቹ ይመሠክራሉ፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡