በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ

FILE - U.N. Secretary General Antonio Guterres, left, and the African Union Commission Chairperson Moussa Faki Mahamat attend a news conference at the African Union Commission headquarters in Addis Ababa, Ethiopia, July 9, 2018.

ከዚህ በተጨማሪም ሁለቱ መሪዎች በኮቪድ 19፣ በነጻ ገበያ እና በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በአሁን ሰዓት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ግጭት እንዲሁም በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያም ሃሳቦችን አንሸራሽረዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ "157 ከባድ መኪኖች ወደ መቀሌ ደርሰዋል፡፡ ስለዚህ ሰብዓዊ ድጋፎች ውጤታማ በሆነ መልኩ በድጋሚ እየጀመሩ ነው፡፡ ምናልባት የምንፈልገውን ያህል ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይሄ ጥሩ ምልክት ነው፡፡ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በረራዎች ከአዲስ አበባ መቀሌ በድጋሚ ተጀምረዋል፡፡ ስለዚህ ወደ ፊት ቀና የሆነ ውይይት ሊመጣ እንደሚችል የሚያመላክቱ ትናንሽ ተስፋዎች አሉ፡፡” ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በበኩላቸው የቀድሞውን የናይጄርያ ፕሬዘዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆን በአፍሪካ ተፋሰስ ሃገራት በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ ላይ አተኩረው እንዲሰሩ ልዩ ልዑክ አድርገው መላካቸውን የገለጹ ሲሆን "እስካሁን ድረስ 3 ጊዜ ተመላልሷል፡፡ ሁለቱንም አካላት አዳምጧል፡፡ መንግስት ሕውሃት ወደ ድንበሩ እንዲመለስ ይሻል፡፡ በተጨማሪም የአብይ አሕመድ መንግስትን ሕጋዊነት እንዲቀበልና እውቅና እንዲሰጥ ይሻል፡፡ በሌላ በኩል ሕውሃቶች የስብዓዊ አቅርቦት እንዲሻሻል ይፈልጋሉ፡፡ የጉዞ ኮሪደሮች እንዲከፈቱ ይሻሉ፡፡ የኤርትራ ኃይሎች ለቀው እንዲወጡ እና በክልሉ የሕዝብ አገልግሎቶች እንዲመልስም ይፈለጋሉ፡፡ በሰፊው ካነሳነው በሁለቱም አካላት በኩል እነዚህ ነገሮች ናቸው የሚነሱት፡፡ ከሁለቱም ጋር መነጋገራችንን ብንቀጥልም አለመታደል ሆኖ መሬት ላይ ግን ጦርነቱ ቀጥሏል፡፡ በእርግጥ ከሰሞኑ ግንባር ላይ በጦርነቱ ቀጠና መረጋጋት እየወረደ መሆኑን አይተናል፡፡ ነገር ግን ይሄ ሁኔታ በጥልቅ ያሳስበናል፡፡" ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ስብሰባ
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:01 0:00

XS
SM
MD
LG