ዋሺንግተን ዲሲ —
እንኳን ለብርሃነ-ትንሣዔው አደረሣችሁ፤ የተከበራችሁ የክርስትና ምዕመናን፡፡
ከላይ የተያያዘው የድምፅ ፋይል የቪኦኤን የቅዳሜ ምሽት የፋሲካ ልዩ ዝግጅት የያዘ ቅንብር ነው፡፡
የአባቶች መልዕክቶች፣ ቁም-ነገር አዘል ውይይቶች፣ መንፈሣዊ መዝሙሮች፣ ለአውደ-ዓመት የተዜሙ ጣዕመ-ዜማዎች በአማርኛ እንዲሁም ደግሞ ከእንግሊዝኛም ወንጌላዊ መዝሙሮች ተካትተውበታል፡፡
የቅዳሜ ምሽት "ከዚህም ከዚያም" እና "የሙዚቃ ቃና" ናቸው ቅንብሩን በጋራ ያሰናዱት፡፡
ፕሮግራሙን ያዘጋጁትና አብረዋችሁም የሚዘልቁት ሰሎሞን አባተና ደሣለኝ መኮንን ናቸው፡፡
እንኳን አደረሣችሁ፤ መልካም ፋሲካ
ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፤ ይዝናኑ