በፖድካስቱ ላይ፣ ፖለቲካንና ምጣኔ ሀብትን እንዲሁም ጤናማ ግንኙነቶችን የተመለከቱ ውይይቶች ይደረጋሉ።
በተጨማሪም፣ በሥርዓተ ጾታ ላይ ምርምር የሚያደርገው ተቋሙ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ፣ በቅርብ አጋሮቻቸው ጥቃት በሚደርስባቸው ሴቶች ላይ በማተኮር፣ ጥቃቱን ለመከላከል ያስችላሉ ያላቸውን የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብሮች ማዘጋጀትን ጨምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን አድርጓል።
የተቋሙን መሥራች እና የሥርዓተ ጾታ ተመራማሪ ሐና ለማን አነጋግረናል ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።