የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው፣ የአገሮች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ በተለይም መድኃኒትን የሚቋቋም ቲቢን የመከላከል ጥረት የሚያሳድጉ ቅስቀሳዎችን ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ በአፍሪካ በተለይም ደግሞ በኢትዮጵያ፣ መድኃኒትን የተላመደ ቲቢ ከባድ ስጋት ደቅኗል።
በኦሃዮ ግዛት ዩኒቨርስቲ፣ ዓለም አቀፉ የግሎባል ዋን ሄልዝ ተነሣሽነት መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኾኑት ወንድወሰን አበበ /ፕሮፌሰር/፣ “ኢትዮጵያ በሳምባ ነቀርሳ ሕመም እና ስርጭት፣ ከዓለም ሰባተኛ ናት፤” ይላሉ። ፕሮፌሰር አበበ፣ ቲቢን ጨምሮ የሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመቆጣጠር፥ ተቋማት፣ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች እና አገሮች፣ በተመሳሳይ ግብ እና ፖሊሲ ሊመሩ እንደሚገባ ያሳስባሉ። በተጨማሪም፣ ቲቢ ከሰው ወደ እንስሳ፣ ከእንስሳ ወደ ሰው ሊተላለፍ የሚችል በመኾኑ፣ የእንስሳት እና የአካባቢ ጤና በጥምረት መታየት እንዳለበት አሳስበዋል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/