በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የላቁ የህክምና ቴክኖሎጂዎች እና መጭው የህክምና ዘርፍ


የላቁ የህክምና ቴክኖሎጂዎች እና መጭው የህክምና ዘርፍ
please wait

No media source currently available

0:00 0:18:30 0:00

ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና የላቁ የህክምና ምርምሮች ድረስ፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በጤና አጠባበቅ አቀራረብ ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ እና ለውጥ እያመጣ ይገኛል። ታዛቢዎች ቀጣዮቹ ዓመታት ቴክኖሎጂው በህክምናው ዘርፍ ላይ እጅግ ግዙፍ የሆነ ለውጥ የሚያመጣበት ይሆናል ሲሉ ይተንበያሉ። በተለይም ሰው ሰራሽ ልህቀት የምርምራ እና የህክምና እቅዶችን ማዘጋጀትን፣ በሽታዎች እና ቀዶ ጥገናዎች በሮቦቶች እንዲደገፉ ማድረግን ጨምሮ እጅግ ብዙ ለውጦችን አካቶ ይዟል። ሰው ሰራሽ ልህቀት ከዚህ በተጨማሪም የሰዎችን በሽታ አስቀድሞ በመለየት እና ዘረመላቸውን በመውሰድ ለግለሰቦቹ ተስማሚ የሆነ የጤና እንክባካቤ ማዘጋጀትን የመሳሰሉ ነግሮች በቀጣይ አስር ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚያሳካቸው ነገሮች መሆናቸውን በዩናይትድ ስቴትስ ዩታ ዩኒቨርስቲ የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG