በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ባህላዊ ህክምናዎች


የአፍሪካ ባህላዊ ህክምናዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:00 0:00

በዚኽ ሳምንት “ኑሮ በጤንነት” ስለ ባህላዊ መድኃኒቶች ደኅንነት፣ አጠቃቀም እና ውጤታማነት እንቃኛለን፡፡

ባህላዊ ሕክምና፥ አካላዊ እና አዕምሯዊ ሕመሞችን ለመመርመር፣ ለመከላከል እና ለማከም የሚውሉ የተለያዩ መንገዶችን ያካተተ ነው፡፡ በሕንድ ከሚገኘው አዩርቤዳ፣ እስከ የቻይና መድኃኒቶች እና የአፍሪካ ባህላዊ ሕክምናዎች...ወዘተ አብዛኛው የዓለም ማኅበረሰብ አሁንም ድረስ የሚጠቀምባቸው ናቸው፡፡

በዓለም የጤና ድርጅት ሥር የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፉ የባህል ሕክምና ማዕከል፣ ከዓለም 88 በመቶ የሚኾኑ ሀገራት፣ እንደ አኩፓንቸር ያሉ የመርፌ ሕክምናዎችን፣ ባህላዊ ቅጠላ ቅጠሎችንና ዮጋን የመሳሰሉ ባህላዊ ሕክምናዎችን ይጠቀማሉ፤ ሲል አስታውቋል፡፡

በተለይ በአፍሪካ፣ ባህላዊ ሕክምናዎች ባላቸው የተሻለ ተደራሽነት እና ዋጋ ምክንያት ብዙዎች ይጠቀሟቸዋል፡፡ ይኹን እንጂ ሕክምናው፣ ለጤና አስጊ የሚኾንባቸው መንገዶች እና አጋጣሚዎችም ይስተዋላሉ፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG