በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የበሽታ መከላከል ሥርዐት መቆጣትን ተከትሎ የሚመጡ ብግነቶች እና ሕመሞች


የበሽታ መከላከል ሥርዐት መቆጣትን ተከትሎ የሚመጡ ብግነቶች እና ሕመሞች
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:00 0:00

የአንጓ ብግነት ወይም የሰውነት የበሽታ ተከላካይ ሥርዐት መቆጣት“Rheumatic”(ሩማተክ) በሽታዎች ፥ በመገጣጠሚያዎች፣ በጡንቻ፣ በአጥንት እና በተለያዩ የሰውነት አካላት ላይ ሕመምን ያስከትላል። የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የአርተራይተስ ቁርጥማት እና የመላ አካል ቁመና እና የቆዳ በሽታዎች ተቋም፣ በዓለም ላይ፣ ከ100 በላይ የሰውነት ብግነት በሽታዎች ስለመኖራቸው አስታውቋል።

አብዛኛውን ጊዜ፣ እነዚኽ ሕመሞች፣ “አርተራይተርስ” እየተባለ በሚጠራው የመገጣጠምያ ብግነት እና ቁርጥማት ውስጥ ይካተታሉ፤ ኩላሊትን፣ ሳምባን፣ ልብንና አንጎልን የሚያጠቁት ሉፐስ እና ሪህ የመሳሰሉት ሕመሞችም የሚጠቃለሉትም በዚኽ ውስጥ ነው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የኑሮ በጤንነት - ሳምንታዊ የጤና መሰናዶ ይከታተሉ።
XS
SM
MD
LG