በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጥቁሮች ጥበብ እና የባህል ውክልና ላይ የምትሠራው ኢትዮጵያዊት ሰዓሊ


የጥቁሮች ጥበብ እና የባህል ውክልና ላይ የምትሠራው ኢትዮጵያዊት ሰዓሊ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:23 0:00

ነፃነት ተስፋዬ ወይም ኔት፣ ነዋሪነቷን በሰሜን ካሊፎርኒያ ግዛት ያደረገች፣ የግራፊክስ እና የገላጭ ሥዕሎች ባለሞያ፣ እንዲሁም የኮከብ ስቱዲዮ መሥራችም ናት። የሚበዙት ሥራዎቿ፥ በጥቁርነት፣ በመብት እና በባህል አካታችነት ዙሪያ ያተኩራሉ።

“ኢትዮጵያ እና የጋቢ ታሪክ” የተሰኙ፣ ሁለት የልጆች ገላጭ መጻሕፍትን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያዘጋጀችው ነፃነት፣ ሥራዋን በቀጣዮቹ ወራት ለአንባብያን ለማድረስ፣ አሳታሚ ተቋማትን አነጋግራ ጨርሳለች፡፡

በሌላ በኩል፣ ሥራዎቿ፣ በሰሜን ካሊፎርኒያ በሚገኘው የ‘ደ ያንግ' ቤተ መዘክር ስብስብ ውስጥ ከሰሞኑ ተካባች ኾነውላታል።

በመጪው የአውሮፓውያኑ ዐዲስ ዓመትም፣ በአፍሪካ አሜሪካውያን “የታሪክ ወር” ላይ ለሽያጭ የሚቀርቡ የልብስ ኅትመቶች፣ በግዙፉ የዩናይትድ ስቴትስ የልብስ እና የጅምላ ሻጭ ተቋም አማካይነት ለገበያ እንደምታቀርብ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቃለች፡፡

XS
SM
MD
LG