በእንግሊዝኛ ስያሜው Girls Gotta Run ‘ገርልስ ጋት ቱ ረን ’ በግርድፍ ትርጉሙ "ልጃገረዶች ይሩጡ" የተሰኘው ግብረ ሰናይ ተቋም ከ15 ዓመታት በፊት የተመሰረተ ሲሆን፤ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ልጃገረዶች ለያለእድሜ መዳር ከተጋለጡባቸው እና ሁለተኛ ደረጃ ሳይደርሱ ትምህርት ከሚያቋርጡባቸው አካባቢዎች መካከል ሁለት ከተሞችን በመምረጥ ይንቀሳቀሳል።
ተቋሙ በአርሲ በቆጂ እና በወላይታ ሶዶ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ልጃገረዶች በአትሌቲክስ እንዲሳተፉ በትጥቅ እና በስልጠና በማገዝ እንዲሁም በምግብ፣ በትምህርት እና በሌሎች የሕይወት ክህሎት ሥልጠናዎችን በመስጠት ያበቃል።
በተጨማሪም ለእናቶች የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት በማዘጋጀት ሴቶች እራሳቸውን እንዲችሉ ያግዛል። ኤደን ገረመው የተቋሙን የሶዶ ሥራ አስኪያጅ እና ተጠቃሚዎችን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅታለች።
መድረክ / ፎረም