በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንጋፋው ተስኪ ጊ የበረራ ትምህርት ቤት አዳጊ ጥቁሮችን በነጻ እያሠለጠነ ነው


አንጋፋው ተስኪ ጊ የበረራ ትምህርት ቤት አዳጊ ጥቁሮችን በነጻ እያሠለጠነ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:12 0:00

በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው ተስኪ ጊ አላባማ፣ ጠንካራ የበረራ ባለሞያዎች የወጡበት ስፍራ ነው። አሜሪካ፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በነበራት ተሳትፎ፣ በአየር ኀይሉ ያገለገሉ 900 ጥቁር አሜሪካውያን ወታደሮችን አሠልጥናበታለች፡፡ በዚኹ አንጋፋ ትምህርት ቤት የተሰየመው በዲትሮይት የሚገኘው ቤተ መዘክር እና ኮል ማን ኤ ያንግ ሙኒሲፓል የበረራ ትምህርት ቤት፣ ጥቁር አሜሪካውያን አዳጊዎች ነጻ የበረራ ሥልጠና እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የተስኪ ጊ ማሠልጠኛ ተመራቂ የኾኑት ጥቁር አሜሪካዊው ኮሎኔል ጆ ቻርለስ፣ በሁለተኛው ዙር የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ጣሊያንን ተዋግተዋል። በጎርጎርሳውያኑ 1950 ዓ.ም. በዚያው በዐዲስ አበባ ማረፋቸውም በታሪክ ሰፍሯል። በአሶሺየትድ ፕሬስ የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG