የሁለተኛ አመት የኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪ የሆነችው ሊዲያ ሰለሞን፤ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እና እድሜያቸው ከሰላሳ ዓመት በታች ለሆኑ ወጣቶች የስነልቦና ድጋፍ የሚያገኙበት የማኅበራዊ ሚዲያ የምክር አገልግሎት ጀምራለች። LYSSA (ሊሲያ) ሥራውን የጀመረው ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት በቴሌግራም መተግበሪያ በኩል ነበር። ሊዲያ ከሌሎች ሰባት የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ጋር በመጣመር ሊዲያ ለወጣቶች ነፃ የመስመር ላይ የምክር አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል።
በሊሲያ ካሉ በጎ ፈቃደኞች የምክር ቤት አባላት መካከል አንዱ ቢኒያም ከድር ይህ አገልግሎት የመንፈስ ጭንቀት ላለባቸው ወጣቶች፣ በራስ የመተማመን መንፈስ እና ተስፋ ለሚቆርጡ ወጣቶች ትልቅ እገዛ ሆኗል ይላል። ኤደን ገረመው ዝርዝሩን ይዛለች።