ገባሬ ሠናይ ተቋማቸው፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ 50 ተማሪዎች የሥራ ዕድል እንዲያገኙ ማስቻሉን የገለጹት አቶ ፈቃዱ፣ የወጣቶች ፍላጎት እና የቀጣሪዎች ዐቅም የሚጣጣም እንዳልኾነ ይናገራሉ፡፡
ይህን ክፍተት በማጥበብ ረገድ፣ “የስ ኢትዮጵያ”፥ አንድ ተመራቂ ተማሪ ሥራ እስኪያገኝ ድረስ፣ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ በበጎ ፈቃድ የሚያገለግልበትን አማራጭ ያመቻቻል፤ ሌሎች ሥልጠናዎችንም ይሰጣል፡፡ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ውጭ ሀገር የሚጓዙ ተማሪዎችን የስፖንሰርሽፕ እና የማረፊያ ጥያቄዎችም ላይ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
የ“የስ ኢትዮጵያ” መሥራች አቶ ፈቃዱ፥ “ወጣቶች ከበጎ ፈቃድ እና ከትስስር መድረኮች በእጅጉ ሊጠቀሙ ይችላሉ፤” ይላሉ፡፡
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/