በኢትዮጵያ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በተከሠቱ፣ ሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች የተነሣ፣ አእላፋት ዜጎች ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለዋል። ግጭት እና ረኀብ፣ የብዙዎችን ሕይወት አደጋ ላይ ጥሏል። እኒኽን መሰል ክሥተቶች፣ በሕፃናት ላይ አስከፊ ሥነ አእምሯዊ ጠባሳ እና ሥነ ልቡናዊ ሠቆቃ ይተዋሉ።
ሕፃናት፥ ከድኅረ አደጋ ሠቆቃ እንዲወጡ፣ ለራሳቸውም ኾነ ለአገራቸው ተስፋ እንዲኖራቸው ለማገዝ የሚረዱ፣ የሕፃናት መጻሕፍትን ጽፎ ለማሳተም፣ የተወሰኑ የሥነ ልቡና ባለሞያዎች፣ ልዩ ልዩ ታሪኮችን ማሰባሰብ ጀምረዋል።
ኤደን ገረመው፣ የእንቅስቃሴውን መሥራች ረዳት ፕሮፌሰር ፍሬው ከፍያለውን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች።