በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከራሷ ችግር በመነሳት ለሃበሻ ጸጉር ተስማሚ የሆነ ምርት የሰራችው - ሩቲ ኦስማን


ከራሷ ችግር በመነሳት ለሃበሻ ጸጉር ተስማሚ የሆነ ምርት የሰራችው - ሩቲ ኦስማን
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:02 0:00

ሩቲ ኦስማን ነዋሪነቷን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገች የስነ ውበት ባለሞያ ናት፡፡ ለቆዳ በሽታ መፍትሄ እንዲሆናት በሃኪም ታዞላት ትወስደው የነበረው መድሃኒት ሙሉ ለሙሉ ጸጉሯን እንዲረግፍ እንዳደረገው ትናገራለች።

ይሁን እንጂ ጸጉሯን ለመንከባከብ ብላ የገዛቻቸው ምርቶች በሙሉ ‘ምንም ዓይነት ለውጥ አላመጡልኝም’ ትላለች። ሩቲ ያላትን የስነ- ውበት እውቀት በመጠቀም ለሃበሻ ጸጉር የሚሆኑ የጸጉር ቅባት፣ ሳሙና፣ ማለስለሻ እና ሌሎች ምርቶችን ሺዋን በተሰኘ የንግድ መለዮ ለገበያ ማቅረብ ችላለች።

ሩቲ በአብዛኛው ገበያ ላይ ያሉ ምርቶች ለአውሮፓዊያን፣ ህንዶች እና እንዲሁም እጅግ በጣም ከርዳዳ ለሆኑ አፍሪካዊያን የጸጉር ዓይነቶች የተሰሩ እንጂ መሃከል ላይ ለሚገኘው የሃበሻ የጸጉር ላይ ተሞክረው የተመረቱ አለመሆናቸውን ትናገራለች።

/ሩቲ ኦስማን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረገችውን ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG