በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለ አጓጊው የፀሐይ ግርዶሽ ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች


ስለ አጓጊው የፀሐይ ግርዶሽ ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:56 0:00

ዛሬ ሰኞ፣ መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሜክሲኮ አንሥቶ፣ በአሜሪካ የሚገኙ 15 ግዛቶችን አቋርጦ ወደ ካናዳ የሚያልፍና እስከ አራት ደቂቃ የሚቆይ ሙሉ የፀሐይ ግርዶሽ እየተጠበቀ ይገኛል። ክሥተቱን ከ36 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ያዩታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከ15 ውጪ የተቀሩት የአሜሪካ ግዛቶች፣ ሙሉ ግርዶሹ ይታይባቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ ግዛቶች እንዳላቸው ርቀት ከፊል ግርዶሽን ያያሉ። ሳይንቲስቶች እና የጤና ባለሞያዎች፣ ሰዎች በ20 ዓመት አንዴ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የሚታየውን የተፈጥሮ ክሥተት ለማየት፣ በናሳ የጠፈር ምርምር ማዕከል ማረጋገጫ የተሰጣቸውን መነጽሮች ብቻ እንዲጠቀሙና መኪና ከመነዳትም እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ክሥተቱ ከተለምዶ ውጭ በመኾኑ፣ የዱር እና የቤት እንስሳት እንግዳ ድምፆችን ሊያሰሙና ያልተለመዱ ኹኔታዎችን ሊያሳዩ እንደሚችልም ይጠበቃል። በናሳ የጠፈር ሳይንስ ተመራማሪው ዶር. ብርሃኑ ታፈሰ ቡልቻ፣ ይህ ወቅት፣ ለሳይንሳዊ ምርምር አጓጊ እና ከባድ የሥራ ወቅት እንደኾነ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ አጋርተዋል። ያነጋገረቻቸው ኤደን ገረመው ናት። ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG