በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቤተ እስራኤላዊው አባት ለዘጠኝ ዓመት የታገተው ልጃቸው እንዲለቀቅ እየተማፀኑ ነው


ቤተ እስራኤላዊው አባት ለዘጠኝ ዓመት የታገተው ልጃቸው እንዲለቀቅ እየተማፀኑ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:05 0:00

በጎርጎሮሳውያኑ መስከረም 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በሐማስ ታጣቂ የታገተው ቤተ እስራኤላዊው አቪራ መንግሥቱ፣ ባለፈው መስከረም ወር ዘጠነኛ ዓመቱን አስቆጥሯል። የአቪራ መንግሥቱን ምስል፣ ባለፈው ዓመት ጥር ወር 2015 ዓ.ም. ላይ፣ በተንቀሳቃሽ ቪዲዮ ያሳየው ሐማስ፣ ታጋቹ በሕይወት መኖሩን አረጋግጧል፡፡ በ28 ዓመቱ የታገተው ወጣቱ፣ አኹን 36ኛ ዓመቱን ይዟል።

የአቪራ መንግሥቱ ቤተሰቦች፣ ልጃቸው ወደ ቤቱ እንዲመለስ ለረዥም ዓመታት በተለያዩ መልኮች ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በአኹን ሰዓት እስራኤል፣ በጥቅምት ሰባቱ የሐማስ ድንገተኛ ማጥቃት የታገቱ ግለሰቦችን ለማስለቀቅ በምታደርገው ጥረት ውስጥ፣ ልጃቸው አቪራ ይካተት ዘንድ፣ ቤተሰቦቹ እየተማፀኑ ይገኛሉ።

ኤደን ገረመው፣ የአቪራ መንግሥቱን ወላጅ አባት አቶ አየሊ መንግሥቱንና በኢትዮጵያ የእስራኤል ምክትል አምባሳደር ቶመር ባርላቪን አነጋግራ ያሰናዳችው ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።

XS
SM
MD
LG