No media source currently available
"ዘ ላስት ኢንኩቤተርስ ኦፍ ባዮ ዳይቨርስቲ" ወይም "የመጨረሻዎቹ የብዝኀ ሕይወት ማበልጸጊያዎች" የተሰኘ የፎቶ ግራፍ ዐውደ ርእይ፣ ከሳምንታት በፊት በዐዲስ አበባ ለእይታ ቀርቦ ነበር፡፡ ዐውደ ርእዩ በይዘቱ፣ በአካባቢ ጥበቃ ላይ አተኩሯል። የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ፥ ከኅሊና እና በኢ.ኦ.ተ. ቤተ ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የቤተ ክርስቲያን ደን ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ ከኾኑት አቶ ተዋናይ ሰይፈ ሥላሴ ጋራ ቆይታ አድርጓል፡፡