በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዊልቸር የተወጠነው የአፍራህ “ኦፕን ቴክኖሎጂስ”


በዊልቸር የተወጠነው የአፍራህ “ኦፕን ቴክኖሎጂስ”
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:20 0:00

“ዓላማዬ የአካል ጉዳተኞችን ሕይወት ማቃለል ነው” - አፍራህ ሁሴን

አፍራህ ሁሴን፣ የሦስተኛ ዓመት የዐዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተማሪ እና የፈጠራ ባለሞያ ናት። የኹለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለች፣ በዕረፍት ጊዜ ዊልቸር ተጠቃሚ አካል ጉዳተኛ ጓደኛ ነበራት፡፡ የትምህርት ቤት ጓደኛዋ፣ በአካላዊ እንቅስቃሴ ውሱንነት ምክንያት ከክፍል ለመውጣት የሚሳነው ነበር፡፡ “ችግር የፈጠራ እናት ናት” እንዲሉ፣ የጓደኛዋ እክል፣ አፍራህን፣ ደረጃ ለመውጣት እና ለመውረድ የሚያስችል ዊልቸር እንድትሠራ ምክንያት ኾናት።

አፍራህ፣ በዚኹ የፈጠራ ሥራዋ፣ በ2012 ዓ.ም. በስቴም ፓወር እና በትምህርት ሚኒስቴር አማካይነት በተዘጋጀ የፈጠራ ሥራ ውድድር ላይ በዊልቸር ግኝቷ ተሳትፋ አንደኛ ለመውጣት በቅታለች። ኾኖም፣ ዊልቸሩን ለገበያ ለማውጣት የሚያስችል፣ የማሻሻጫ እና የምርት አቅርቦት ዕድል ባለመኖሩ፣ ቀለል ያሉ የፈጠራ ሥራዎችን ከማቅረብ መጀመር እንዳለባት ተገንዝባለች፡፡

ከትምህርቷ ጎን ለጎን፣ ከታላቅ እኅቷ ጋራ “ኦፕን ቴክኖሎጂስ” የተሰኘ ተቋም መሥርተው፣ የአካል ጉዳተኞችን ሕይወት ሊያቃልሉ የሚችሉ፣ ልዩ ልዩ የፈጠራ ሥራዎችን ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅታቸውን እያጠናቀቁ እንደኾነ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጻለች፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG