በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሀገር በቀል የትምህርት መፍትሔዎች እንዲዳብሩ የሚሠራው ተቋም


ሀገር በቀል የትምህርት መፍትሔዎች እንዲዳብሩ የሚሠራው ተቋም
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:26 0:00

“ሩት ኤንድ ዊንግስ”፣ ከአራት ዓመታት በፊት በሕክምናው እና በትምህርት ዘርፍ ላይ ሲሠሩ በቆዩ የትዳር አጋሮች አማካይነት የተመሠረተ ገባሬ ሠናይ ተቋም ነው። የተቋሙ አጋር መሥራች እና የቦርድ አባል ዶር. ሰርካለም ግርማ፣ በተለያዩ ጥናቶች

እና ምርምሮች ላይ አተኩሮ ሲሠራ በቆየው ኤሊክሰር የተሰኘ የግል ምርምር ተቋም በኩል የተገነዘቧቸው ማኅበራዊ ተግዳሮቶች እና የመፍትሔ ክፍተቶች፣ ለሩት ኤንድ ዊንግስ መመሥረት መነሻ መኾናቸውን ይናገራሉ።

ዶር. ሰርካለም፣ ተቋሙ፣ የግብረ ገብ ትምህርት በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት ጥረት ያደርጋል፤ ብለዋል፡፡ በተጨማሪም፣ የምልክት ቋንቋ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሥራ መገልገያ እንዲኾንና መስማት የተሳናቸውም በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ የሥራ ዕድል እንዲያገኙ እየሠራ መኾኑን አመልክተዋል።

ኤደን ገረመው የተያያዘውን ዘገባ አሰናድታለች።

XS
SM
MD
LG