በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 ሴት ተማሪዎችን በሴት መሪዎች ማብቃት


 ሴት ተማሪዎችን በሴት መሪዎች ማብቃት
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:54 0:00

ከሁለት ዓመት በፊት የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ጽ/ቤት፣ ከአለም አቀፉ ትምህርት ተቋም ጋር በመሆን ሴት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ለማብቃትና ስኬታማ ለማድረግ፤ ከበቁ ሴት አመራሮች ጋር የማጣመርና የምክር (የሜንቶርሺፕ) መርኃግብር ማስጀምሩን አስታውቆ ነበር።

ይህ የምክክር ሂደት በተለያየ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ያሉ ሴቶች በበጎ ፍቃደኝነት እያንዳንዳቸው ከአምስት ሴት ተማሪዎች ጋር በመቆራኘት የሚያስኬዱት ነው።

በዚህ ሂደት ውስጥ ካለፉት ተማሪዎች መካከል አንዷ የሆነች እና በቅርቡ በሜካኒካል ምህንድስና የተመረቀችው ጽዮን መነሻ ይሄ ምክክር እና ክትትል ዕድል ያጋጠመኝ ውስጤ እጅግ በጣም በተዳከመበትና ይሄ ስሜቴም ውጤቴም ላይ ተጽእኖ እያሳደረ በነበረበት ወቅት ነበር ትላለች።

ይሁን እንጂ በዚህ መርሃግብር አማካኝነት ባገኘቻት አማካሪዋ የቅርብ ክትትል እሷም ሆነች ጉደኞቿ በትምህርታቸው መሻሻል፣ በተለያዩ የት/ቤት ዝግጅቶች ላይ አስተባባሪ በመሆን አመራርን መላመድ እና የተለያዩ የህይወት ክህሎቶችን ማዳበር መቻላቸውን ትናገራለች።

XS
SM
MD
LG