ለመሃንዲሶች ነጻ መመራመሪያ ቦታ የሆነው-ነርድ
ከተመሰረተ ሶስት ዓመታትን ያስቆጠረው ነርድ በምህንድስና የተመረቁ ወጣቶች የፈጠራ ስራዎቻቸውን የሚያዳብሩበት የምርምር ማዕከል ነው። ይህ ተቋም 'ምህንድስና ስራ አያስገኝም' የሚል አስተሳሰብ እንዲቀረፍ እንዲሁም መሰረታዊ የሆኑ የሃገሪቱ ችግሮች አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ሮቦቲክስ፣ ኤሌክትሪካል እና ሌሎች የምህንድሰና ዘርፎችን በመጠቀም ለመቅረፍ እየሰራ ይገኛል። የተቋሙ አጋር መስራች ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርጓል። /ዝርዝሩን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ/