በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሜሪላንድ ግዛት የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሊጀመር ነው


በሜሪላንድ ግዛት የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሊጀመር ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:07 0:00

በዩናይትድ ስቴትስ ሜሪላንድ ግዛት በሞንጎሞሪ ካውንቲ የሚገኘው ኖርዝ ዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመጪው የትምህርት ዘመን የአማርኛ ትምህርትን እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በሞንጎሞሪ ውስጥ ብቻ ከ50 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ትምህርት ቤቱ ከእንግሊዘኛ እና ከስፓኒሽ ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አማርኛ ተናጋሪዎች እንደሚማሩ ገልጿል።

ትምህርት ቤቱ በመጪው ነሃሴ ለሚጀምረው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትም ቅጥር እና መሰረታዊ የትምህርት መርጃዎችን በማሰናዳት ላይ የሚገኝ ሲሆን ትምህርቱ ከቋንቋ ባለፈም ታሪክን እና ባህልን ያካተተ እንደሚሆነም የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የትምህርት ቤቱ መመህራን አስታውቀዋል። ከዚህ ተሞክሮ በመነሳት በቀጣይ የቋንቋ ትምህርቱ ወደ ሌሎች ትምህርት ቤቶች የማስፋፍት ህልም እንዳለም የትምህርትቤቱ አስተዳደሮች አስታውቀዋል።

ምንም እንኳን በዩናይትድ ስቴትስ በከፍተኛ ደረጃ ተቋማት ውስጥ የአማርኛ እና የግዕዝ ቋንቋ ትምህርቶች ቢሰጡም በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ግን ይሄ የመጀመሪያው ነው።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG