በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች የአነቃቂ ተናጋሪዎች መብዛትና የማኅበራዊ ቀውስ ስጋት


በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች የአነቃቂ ተናጋሪዎች መብዛትና የማኅበራዊ ቀውስ ስጋት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:34 0:00

በኢትዮጵያ በተለይም በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየበዙ የመጡት “አነቃቂ ተናጋሪዎች እና ንግግሮቻቸው” የውዝግብ ምክንያት እየኾኑ ይስተዋላል፡፡ በሌላው ዓለም፣ አነቃቂ ንግግሮች የተለመዱና በማኅበረሰብ ውስጥም አወንታዊ ሚና እንዳላቸው፣ ባለሞያዎቹ ይናገራሉ፡፡ ይኹንና በአሁኑ ወቅት፣ በኢትዮጵያ፣ በጥናት ሳይደገፉና የማኅበረሰቡን ፍላጎት ታሳቢ ሳያደርጉ እየተሰራጩ እንደሚገኙ ይገልጻሉ፡፡

አነቃቂ ንግግሮቹ፥ ከሞያዊነት፣ ከሓላፊነት እና ከማኅበረሰባዊ ፋይዳ አኳያ ሲመዘኑ፣ ችግሮች እንዳሉባቸው የሚያስረዱት ባለሞያዎቹ፣ የሚከታተሏቸውን ወገኖችም፣ እንደ ድባቴ ላሉ የአእምሮ ጭንቀት ሕመሞች በመዳረግ፣ ማኅበራዊ ቀውስ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ያመለክታሉ፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ይህን ዘገባ በሚያጠናቅርበት ወቅት፣ በአነቃቂ ንግግሮች ላይ በተመሠረተ የሕይወት ክህሎት ሥልጠና ላይ እየሠሩ ያሉ ግለሰቦችን ሐሳብ ለማካተት ያደረገው ጥረት፣ ፈቃደኛ ባለመኾናቸው ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

ዝርዝሩን ከቀጣዩ ፋይል ይከታተሉ፡፡
XS
SM
MD
LG