በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኢትዮጵያን በስፌት ሥራ ለዓለም ማስተዋወቅ እፈልጋለሁ” - የቱባ በአራራት መሥራች


“ኢትዮጵያን በስፌት ሥራ ለዓለም ማስተዋወቅ እፈልጋለሁ” - የቱባ በአራራት መሥራች
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:49 0:00

የኪነ ሕንፃ ባለሞያዋን አራራት ታምራት ከኹለት ዓመት በፊት፣ ቱባ በአራራት የተሰኘ የጥበበ እድ የመሠረተች ሲኾን፤ ተቋሟ በልዩ ልዩ ቀለማት፣ መጠንና ቅርጽ የተዋቡ ባህላዊ የስፌት ሥራዎችን ለገበያ ያቀርባል፡፡

የድርጅቱ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አራራት ታምራት፣ ኪነ ሕንፃን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተማረችበት ጊዜ፣ የሰፌድ እና የልዩ ልዩ ስፌት ክህሎቶችን፣ ከአካባቢው ማኅበረሰብ ለመቅሰም ዕድል ማግኘቷን አውስታለች፡፡ በጥበበ እድ ተቋሟ፣ ኀምሳ የሚደርሱ ሞያተኞችን ቀጥራ የምታሠራ ሲኾን፣ ኹለት ቅርንጫፎችንና አንድ የሥራ ማዕከልም ከፍታለች፡፡

“የስፌት ሥራ የሚሠሩ ባለሞያዎችን ፍለጋ በየመንደሩ በር አንኳኳ ነበር” የምትለው አራራት፤ ኢትዮጵያን በስፌት ሥራ ለዓለም ማስተዋወቅ እንደምትፈልግ ትናገራለች።

አራራት ታምራትና በተቋሙ የጥበበ እድ እንዲሁም የሠራተኞች አስተባባሪ የኾነችው መቅደላዊት ድማሙ፣ ከጋቢና ቪኦኤ ጋራ ቆይታ አድርገዋል፡፡

XS
SM
MD
LG