በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለካንሰር ታካሚዎች የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ማሰባሰቢያ ባንክ


ለካንሰር ታካሚዎች የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ማሰባሰቢያ ባንክ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:17 0:00

ዶ/ር ሚካኤል ሻውል በሀረማያ ዩኒቨርስቲ ህይወት ፋና ሆስፒታል የካንሰር ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ከዘመናዊ አኗኗር ዘዴ ጋር እየጨመረ ለመጣው የካንሰር ህመም ታካሚዎች ከገንዘብ ድጋፍ ጎን ለጎን ሊደረጉ የሚችሉ ድጋፎችን በተመለከተ በማኅበራዊ ድረገጾች ላይ ግንዛቤ ያስጨብጣሉ።

ሳሙናና የሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎች፣ ከህክምና ሂደቱ ጋር ጋር ተያይዞ ለሚመጡ የጸጉር መርገፍ እንዲሁም ደግሞ የጡት መቆረጥ ድጋፍ ሊሆኑ የሚችሉ ሰው ሰራሽ ጸጉሮች እና ጡት ማስያዣዎች፣ ተጨማሪ ውስጥ ልብሶች አስፈላጊ መሆናቸው ማኅበረሰቡ ሊገነዘብ ይገባል ይላሉ። ዶ/ር ሻውል ከዚህ በተጨማሪም ልክ እንደ የደም ባንክ ሁሉ የጡት ማስያዣ እና ለካንሰር ህሙማን የሚያገለግሉ ቁሶች ባንክ ያሻል ይላሉ።

ዶ/ር ሚካኤል ሻውል ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉትን ቃለመጠይቅ ከተያያዘው ፋይል ያግኙ።

XS
SM
MD
LG