ተቋሙ ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ በጎ ፈቃደኞችን በአስር ክልሎች ውስጥ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የተቋሙ ማዕከላት ጋራ በማቆራኘት ሥልጠናዎችን እየሰጠ ነው። ተቋሙን የመሰረቱት በዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የኤሮኖቲክስ እና የጠፈር ምርምር ድርጅት (ናሳ) ተመራማሪ ዶክተር ብርሃኑ ቡልቻና ባለቤታቸው የሥነሕይወት ኬሚስትሪ ተመራማሪ ዶ/ር ጸጋ እንዲሁምናቸው። ኤደን ገረመው የተቋሙን መስራቾች፣ በጎፈቃደኞችንና የመርሃግብሩ ተሳታፊዎች አነጋግራ ያሰናዳችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።