"አብነት የጎዳና ፎቶግራፍ" - በየጊዜው የሚለዋወጡትን የአዲስ አበባንና የልዩ ልዩ ከተሞችን የዕለት ተዕለት ውሎዎች፣ በደምሳሳው የሚያሳይና የሚሰንድ የፎቶግራፍ ገጽ ነው።
በፎቶግራፍ ከታቢው አብነት ተሾመ፣ ሥራዎቹን በዓለም አቀፍ ደረጃ፥ በኤርትራ፣ ኬንያ፣ ማሊ፣ ሕንድ፣ ጀርመን፣ ቤልጂየም፣ ሮም፣ ፓሪስ እና ኦስሎ ... የታዩለት አርቲስት ነው።
በአሁን ሰዓት፣ ከፎቶግራፍ ባለሞያዋ ስኂን ተዋበ ጋራ፣ በጀርመን ኮሎኝ ሥራዎቹን ለእይታ በማቅረብ ላይ ይገኛል።
አብነት ከጎዳና ላይ ፎቶግራፎች በተጨማሪ፣ ልዩ ልዩ የማስታወቂያ፣ የጉዞ፣ እንዲሁም ለሞዴሎች ራስን መግለጫነት የሚያገለግሉ ፎቶግራፎችንም ያነሣል። አብነት ተሾመ በሥራዎቹ ዙሪያ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርጓል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/