No media source currently available
ዓመታዊው የፍሪደም ሃውስ ዘገባ እንደሚያመለክተው ባለፈው ዓመት ብቻ በ72 ሃገሮች የአጠቃላይ ነፃነት ሁኔታ ቀንሷል። የነፃነት ማሽቆልቆል ከተጀመረባቸው ዓመታትም የከፋው አምና እንደሆነም ዘገባ አክሏል። ጥናት ከተደረገባቸው 195 ሀገሮች 50ዎቹ ነጻ አይደሉም። 59 ደግሞ ከፊል ነጻ ተብለዋል። የከፋ ጭቆና ያለባቸው ሀገራት ሶርያ፣ የቻይናው ቲቤት ራስ ገዝ ክልል፣ ሶማልያ፣ ሰሜን ኮርያ፣ ኡዝቤኪስታንና ኤርትራ እንደሆኑ የፍሪደም ሃአሱ ዘገባ የገልጻል።