በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመከላከያ እና የፋኖ ትጥቃዊ ግጭት በግብርናው ላይ ተጽእኖ እንዳስከተለ ተገለጸ


የመከላከያ እና የፋኖ ትጥቃዊ ግጭት በግብርናው ላይ ተጽእኖ እንዳስከተለ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:54 0:00

በዐማራ ክልል በአገሪቱ የመከላከያ ኀይል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተስፋፋው ትጥቃዊ ግጭት፣ በግብርና ሥራቸው ላይ ተጽእኖ እንደፈጠረባቸው፣ በሰሜን ሸዋ እና በደቡብ ወሎ ዞኖች የሚገኙ አርሶ አደሮች አስታወቁ፡፡ ከዘገየው የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት በተጨማሪ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የተስፋፋው የትጥቅ ግጭት፣ የእርሻ ማሳቸውን በትኩረት እንዳይንከባከቡ እያናጠባቸው እንዳለና ለምርት እጥረትም ሊዳርጋቸው እንደሚችል፣ አስተያየታቸውን የሰጡ አርሶ አደሮች ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ከዐማራ ክልል ግብርና ቢሮ፣ ዝርዝር መረጃዎችን ለማካተት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም፣ ዐዲሱ የዐማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ፣ የጸጥታ ስጋቱ በመኸር ሰብል ልማት ላይ ተጽእኖ እንዳሳደረ፣ ከካቢኔያቸው ጋራ ባካሔዱት ውይይት አረጋግጠዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG