በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የቦልቲሞር ካምፓስ የኢትዮ-ኤርትራውያን የተማሪ ማኅበር ተመሠረተ 


በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የቦልቲሞር ካምፓስ የኢትዮ-ኤርትራውያን የተማሪ ማኅበር ተመሠረተ 
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:48 0:00

ሳሮን ክብከባው እና ዕድላዊት ጋረደው፣ በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ቦልቲሞር ካምፓስ፣ የኢትዮ-ኤርትራውያን ተማሪዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት እንደቅደም ተከተላቸው ናቸው። ማኅበሩ፣ ከመቶ በላይ ንቁ አባላት አሉት። በአሁን ሰዓት ማኅበራቸው፣  ብዙ አባላት ያፈራ ሲኾን፣ በአዕምሮ ጤና፣ በባህል ትስስር እና ማኅበረሰቡን በሚደግፉ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች ላይ፣ በበጎ ፈቃድ እና ገቢ በማሰባሰብ ይሳተፋል። 

ሁለቱ ጓደኛሞች፣ ባለፈው ዓመት ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲገቡ፣ የዩኒቨርሲቲ የኢትዮ-ኤርትራ ማኅበራት በሚያዘጋጇቸው መሰናዶዎች ላይ ለመሳተፍ፣ ከዩኒቨርሲቲያቸው አንዳንዴም ካሉበት ግዛት ራቅ ብለው መጓዝና ብዙ ኪሎ ሜትሮችን መንዳት ነበረባቸው። አሁን ግን፣ በራሳቸው ዩኒቨርሲቲ ውስጥ፣ የኢትዮ-ኤርትራውያን የተማሪ ማኅበር እንዳቋቋሙ፣ ጓደኛሞቹ ሳሮንና ዕድላዊት ይናገራሉ።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG