በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሙርሲ ቋንቋ የተዘጋጀው የመጀመሪያ ተውኔት


በሙርሲ ቋንቋ የተዘጋጀው የመጀመሪያ ተውኔት
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:25 0:00

በኢትዮጵያ የተውኔት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ ነው የተባለ በሙርሲ ቋንቋ የተዘጋጀ ተውኔት እሁድ ሐምሌ 24/2014 ዓ.ም ለዕይታ ቀርቧል። በደቡብ ኦሞ ትያትር ኩባንያ የተሠራው 'ቲራኒያ ኮ ኮይሳኒ' ወይም 'ዳኛው' የተሰኘው ተውኔት በሙርሲ ማኅበረሰብ ላይ ጥናት ተደርጎ የተሠራ መሆኑን የተውኔቱ አዘጋጅ አስተዋይ መለሰ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግሯል።

ከመሪ ገፀባህሪ ጀምሮ አብዛኛውን ቁጥር የያዙት ተዋንያኖች ከዚh ቀደም ምንም ልምድ ያልነበራቸው እና ከማኅበረሰቡ የተውጣጡ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል። “ዓላማችን ኢትዮጵያን በኪነ ጥበብ ዘርፍ ባልታየው መነጸር ማሳየት ነው" ብሏል።

/ ከደቡብ ኦሞ ቲያትር ኩባኒያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስተዋይ መለሰ ጋር የተደረገውን ቆይታ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG