በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማኅበረሰብ የጤና ስጋት - ሄፓታይተስ፤ የጉበት መቆጣት


የማኅበረሰብ የጤና ስጋት - ሄፓታይተስ፤ የጉበት መቆጣት
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:00 0:00

ሄፓታይቲስ የጉበት መቆጣት ሕመም ነው። የጉበት ሕመም ብዙውን ጊዜ “ድምፅ አልባው ገዳይ” እየተባለ ይጠራል። የጉበት ሕመም ያለባቸው ሰዎች፣ በሽታው ገፍቶ እስኪወጣ ድረስ፣ በቫይረሱ መጠቃታቸውን ሳያውቁ፣ እጅግ ቀላል የሚባሉ ምልክቶችን ብቻ ይታይባቸዋል።

ሄፓታይተስ ታዲያ፣ ለየት ባሉ የጤና ኹኔታዎች አልያም ጉበት በአልኮሆል እና በልዩ ልዩ መራዥ ነገሮች ሲጎዳ በተለይም ደግሞ በቫይረሱ ሲጠቃ የሚከሠት ነው።

አምስት ዐይነት የሄፓታይተስ ቫይረስ ያሉ ሲኾን፤ ዐይነት A፣ ዐይነት B፣ ዐይነት C፣ ዐይነት D እና ዐይነት E በመባል ተለይተው ይታወቃሉ። የዓለም ጤና ድርጅት፣ በአፍሪካ 91 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች፣ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ በተሰኙት ገዳይ የጉበት ቫይረሶች መጠቃታቸውን አስታውቋል። ሄፓታይተስ ኤ እና ኢ የተሰኙት ቫይረሶች፣ በተመረዙ ምግቦች እና መጠጦች የተነሣ ሲከሠቱ፤ ሄፒታይተስ ቢ የተሰኘው ደግሞ፣ በግብረ ሥጋ ግንኙነት አማካይነት ይተላለፋል። ሄፓታይተስ ቢ፣ በዓለም ላይ በከፍተኛ ኹኔታ ሰዎችን ከሚያጠቁ የጉበት ሕመሞች መካከል ቀዳሚው እንደኾነ ጥናቶች ያሳያሉ።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው መሰናዶ ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG