በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሰቃቂ ሁኔታዎች ውስጥ ያለፉ ህጻናትን የሚያጋጥማቸው የአዕምሮ መረበሽ 


በአሰቃቂ ሁኔታዎች ውስጥ ያለፉ ህጻናትን የሚያጋጥማቸው የአዕምሮ መረበሽ 
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:00 0:00

የተለያዩ የአለም ክፍሎች በተፈጥሯዊ እና በሰው ሰራሽ ችግሮች እየተፈተኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህም የተነሳ የሰው ልጆች ለመፈናቀል፣ ለስደት፣ ጦርነት፣ ርሃብ እና ሌሎቾ ፈተናዎች ውስጥ ናቸው፡፡ ይህም አካላዊ እና መንፈሳዊ ጤናቸውን በማያናጋት ላይ ይገኛል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት ብቻ በዓለም ዙሪያ ቁጥሩ 3.9 የሚደርስ የአለም ህዝብ ከዚህ አስከፊ የመንፈስ መረበሽ ችግር መጋለጡን በቅርቡ የተካሄዱ ጥናቶች አመላክተዋል፡፡

ይህ ቀደም ሲል የደረሰን አንዳች ከባድ አደጋ ተከትሎ የሚመጣ የአእምሮ ጤና ችግር (ድህረ አደጋ ሰቀቀን)፤ ሰዎች በጦርነት፣ ተገድዶ የመደፈር ጥቃት ሲደርስባቸው፣ አልያም የመኪና እና ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎች ውስጥ ለማለፍ በሚገደዱበት ወቅት የሚከሰት የአዕምሮ ጭንቀት ሲሆን፤ በማንኛውም ሰው ላይ ሊከሰት የሚችል ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜም በዚህ የጤና ችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች ንዴት (ወይም ብርቱ የቁጣ ስሜት) እና ጠብ የመፈለግ ዝንባሌ ሲታይባቸው፤ ወዳጅ የማፍራት ችግር ሊገጥማቸው እና እራስን የማጥፋት ፍላጎት ሊያድርባቸው ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ታዲያ ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን፣ ቤተሰብን እና ማኅበረሰብን ጭምር ለብርቱ ችግር የሚዳርግ ሲሆን፤ ህጻናትም የዚህ ችግር ዋነኛ ገፈት ቀማሾች መሆናቸው ይታወቃል።

ለመሆኑ በጦርነት፣ ስደት፣ አስከፊ ረሃብ እና ሌሎች ችግሮች ውስጥ ያለፉ ህጻናት ምን ዓይነት የስነልቦና ድጋፍ ያስፈልጋቸው ይሆን? በዚህ ውስጥ እያለፉ ያሉ ቤተሰቦችን እንዲሁም ባለሞያ አነጋግረናል፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የኑሮ በጤንነት መሰናዶ ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG