በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አና ዲጂታል ቴክኖሎጂ - በሪፈራል ሕክምና መጉላላትን የማስቀረት ውጥን


አና ዲጂታል ቴክኖሎጂ - በሪፈራል ሕክምና መጉላላትን የማስቀረት ውጥን
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:38 0:00

አና ዲጂታል ጤና ሶሉሽን፣ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዐት በማዘምን ላይ አተኩሮ እየሠራ የሚገኝ ጀማሪ ተቋም ነው። በዋናነትም፥ በሆስፒታሎች መካከል ያለውን የመረጃ መጋራት፣ እንዲሁም በሪፈራል ሕክምና የሚያጋጥም መጉላላትንና የጊዜ ብክነትን ለመቀነስ ይሠራል። ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሌላ ሆስፒታል ለሚላኩ ሕሙማን፣ የሆስፒታል አልጋን ጨምሮ አስፈላጊ አገልግሎቶች የተሟሉላቸው ስለመኾኑ፣ ማረጋገጥ የሚቻልበትን ሥርዐት ይዘረጋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ፣ በስምንት የግል ሆስፒታሎች፣ የመረጃ ማጋራት ወይም ኔትወርኪንግ ሥርዓት መዘርጋት መቻሉን፣ የተቋሙ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሊዲያ ታደሰ፤ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቃለች። ተቋሙ፣ በስምንቱ የግል ሆስፒታሎች ላይ ያለውን የሥርዓት ዝርጋታ ተሞክሮ በመውሰድ፣ በቀጣይ ከጤና ተቋማት እስከ ታላላቅ የመንግሥት ሆስፒታሎች ያሉትን ለማስተሳሰር ወጥኗል።

ከዚኽ በተጨማሪ፣ ለሕሙማን ቀጥተኛ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ መተግበሪያዎችንም ያዘጋጃል። ከሰሞኑም፣ ለስኳር ሕሙማን የሚያገለግል “ጤና ሲቲ” የተሰኘ መተግበሪያ፣ በአንድሮይድ ስልኮች ላይ ይፋ አድርጓል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG