በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ትምህርት እና ልዩ ልዩ ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ማኅበር ሊያቋቋሙ ነው


በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ትምህርት እና ልዩ ልዩ ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ማኅበር ሊያቋቋሙ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:59 0:00

እንደ አውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ2010 የተጀመረው የወጣት አፍሪካዊያን መሪዎች የጉድኝት እና የትሥር መድረክ የሲቪክ፣ የቢዝነስ እና ማኅበረሰብ መሪዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ የታመነባቸውን ወጣቶች ለማሰልጠን እና ለማስተሳሰር በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ቢሮ አማካኝነት እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡

ይህ መርሃግብር የዩናይትድ ስቴትስመንግስት ለአፍሪካዊያን ወጣቶች የሚያዘጋጃቸውየስልጠና ዓይነቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ወጣቶች በተለያዩ የትምህርት እና የአመራር ስልጠናዎች የሚያገኙባቸው ልዩ ልዩ መርሃግብሮች አሉ። አኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ በእነዚህ መርሃብሮች ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የተሳተፉ ሰዎች ቁጥራቸው ወደ 4000 እንደሚደርስ ተሳታፊዎቹ አስታውቀዋል።

አብዛኞቹም ወደ ሃገራቸው ተመልሰው በተለያዩ መንገዶች ማኅበረሰባቸውን ያገለግላሉ። እነዚህ በዚህ ሂደት ውስጥ ያለፉ ወጣቶችን የሚያስተሳሰር፣ ከኤምባሲው የሚወጡ መረጃዎችን ማዕከላዊ በሆነ መልኩ የሚያከፋፍል እንዲሁም ደግሞ በግለሰብ ደረጃ የሚሰሩ ማኅበራዊ አገግሎቶችን በጋራ እንዲሰሩ ለማድረግ፤ ባሳለፍነው በመጋቢት 2015 የመጨረሻው ሳምንት፤ ተመላሾቹ ማኅበር ለመመስረት ተስማምተዋል። በዚህ መሰረትም ኮሚቴ ተቋቁሞ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን በዚህ መልኩ አገልግሎት እያበረከቱ ያሉ ሁለት ወጣቶች ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG