የቤት ውስጥ ጭስ እና የጨቅላ ሕጻናት የመተንፈሻ ችግር
ኢትዮጵያ ውስጥ የሕጻናት ህይወት ከሚቀጥፉ እና ለድንገተኛ ሞት ከሚዳርጉ በሽታዎች አንዱ የመተንፈሻ አካላት ችግር ነው። በመኖሪያ ቤቶች ውስጥ የሚነዱ ከእንጨትና ከከሰል የሚወጡ ጭሶች እንዲሁም ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከተሞች እየተለመደ የመጣው በቤት ውስጥ ሺሻ የማጨስ ልማድ በሕጻናት በተለይም በጨቅላ ህጻናት ሕይወት ላይ ከፍተኛ አደጋ ጋርጧል ይላሉ በጅማ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የህጻናት ሃኪም የሆኑት ዶ/ር መሃመድ በሽር። /ዝርዝሩን ከተያያዘው የምስል ፋይል ይከታተሉ/