ቀደም ሲል፣ በአእምሮ ጤና እክል ይቸገር የነበረው፣ ናይጄሪያዊው የፎቶግራፍ ጥበብ ባለሞያ ኤሚካ ዲንዱ፣ በዳንስ ስሜቱን ማሻሻል እንደቻለ ይናገራል፡፡ ኤሚካ ሣልሳ እና አፍሮ ካሪቢያን ሙዚቃዎችን በመጠቀም፣ በናይጄርያ ዋና ከተማ አቡጃ፣ ሰዎች በነፃ የሚዝናኑበት ሳምንታቲ፣ የዳንስ ድግስ ማዘጋጀት ከጀመረ አምስት ዓመት ኾኖታል፡፡ ብዙዎች በዳንሱ ላይ በመሳተፋቸው፣ ያለባቸውን የአእምሮ ጤና እክል ለማስወገድ እንዳስቻላቸው ይናገራሉ፡፡
የሮይተርስን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡