በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለግጭት አካባቢ  ባለሞያዎች ሥነ ልቡናዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል - ባለሞያዎች 


ለግጭት አካባቢ  ባለሞያዎች ሥነ ልቡናዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል - ባለሞያዎች 
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:12 0:00

የትግራይ ክልልን መነሻ አድርጎ በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሔደው ጦርነት ወቅት፣ በልዩ ልዩ ዘርፎች ላይ ተሠማርተው ማኅበረሰቡን ያገለገሉ ሠራተኞች፣ ያለፉባቸውና የተመለከቷቸው ሰቅጣጭ ኹኔታዎች፥ ለድኅረ አደጋ ሠቆቃ ሊያጋልጥቸው እንደሚችል፣ የሥነ ልቡና ባለሞያዎች ይናገራሉ። ተፈናቃዮችን በሚረዱ ገባሬ ሠናይ ድርጅቶች ውስጥ የሚሠሩ የሰብአዊ ድጋፍ ሠራተኞች እና ጋዜጠኞች፣ እንደ አብነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

በባሕር ዳር እና በመቐለ የሚገኙ የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢዎች፣ በሁለት ዓመቱ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት፣ ስምሪተኞች ኾነው የቆዩ ባለሞያዎች፣ የሥራ ውሏቸው በሥነ ልቡናቸው ላይ ያሳደረባቸውን ጫና እንዲያጋሯቸው ጠይቀዋል፡፡
የጦርነቱ ወቅት ባለሞያዎቹ፣ የተመለከቷቸው ሰቅጣጭ ጉዳቶች፣ እስከ አሁን ድረስ ተቆራኝቷቸው፥ ለዘለቀ ጭንቀት፣ እንቅልፍ ማጣት እና ተስፋ መቁረጥ እንዳጋለጣቸው ተናግረዋል።
በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ አእምሮ ክፍል ባልደረባ ዶር. ዐወቀ ምሕረቱ፣ አብዛኛውን ጊዜ፣ በጦርነቱ የተፈናቀሉ እና የተጎዱ ዜጎችን በማገዝ ሥራ ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎች ራሳቸው፣ የሥነ ልቡና ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ከግምት ስለማይገባ ይዘነጋል፤ ይላሉ።
ችግሩ በጊዜ ካልታከመ፣ ለድኅረ አደጋ ሠቆቃ(PTSD) እንደሚያጋልጥ ዶር. አወቀ ይናገራሉ። አክለውም፣ መንግሥት እና በጤና ሥርዐቱ ውስጥ የሚሠሩ ተቋማት፡- የጦር ሠራዊት አባላት፣ ግጭትን የሚዘግቡ ጋዜጠኞች፣ የሕክምና አባላት፣ ገባሬ ሠናይ ሠራተኞች እና የመሳሰሉት፣ በዘላቂነት የሚረዱበት ሥርዐት ሊዘረጋላቸው እንደሚገባ ያመለክታሉ፡፡
አሁን ላይ “በየቦታው የተጀመሩ ሥራዎች አሉ፤” የሚሉት ዶር. አወቀ፣ በእንዲህ ዐይነት ሥራዎች ላይ የሚመደቡ ሰዎች፣ ሰፋ ያለ የዕረፍት ጊዜ፣ የፈረቃ ሥራ፣ እንዲሁም ስሜታቸውን የሚያጋሩባቸው ስልቶች እና መርሐ ግብሮች ሊኖሩ እንደሚገባ ይመክራሉ።
XS
SM
MD
LG