በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከማኅበራዊ መገናኛ አንቂነት ወደ ንግዳዊ ተቋም ባለቤትነት - ፎዚያ አወል


ከማኅበራዊ መገናኛ አንቂነት ወደ ንግዳዊ ተቋም ባለቤትነት - ፎዚያ አወል
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:34 0:00

ፎዚያ አወል፣ ከአዳማ ዩኒቨርስቲ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተመርቃለች። ከስምንት ዓመት በፊት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ሳለች፣ ልዩ ልዩ የሂጃብ አለባበሶችንና የሥነ ውበት ምክሮችን በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ ላይ ማጋራት የጀመረችው ፎዚያ፣ በጊዜ ሒደት እጅግ ብዙ ተከታዮችን በማፍራት፣ በትስስር መድረኩ ተጽዕኖ ፈጣሪ እየኾነች መጥታለች፡፡

በትምህርት የቀሰመችውን ዕውቀት እና ኢንስታግራምን ጨምሮ በሌሎች የማኅበራዊ መገናኛ አማራጮች ያገኘችውን እውቅና በመጠቀም አናናስ የተሰኘ የንግድ እና የብራንዲንግ ተቋም ከጓደኛዋ ጋራ መሥርታለች፡፡ ፎዚያ በዚኹ ተቋሟ፣ የማስተዋወቅ እና የብራንዲንግ(ንግዳዊ መለዮ ግንባታ) አገልግሎት ትሰጣለች። በቀጣይም፣ የሙስሊም አልባሳት የፋሽን ሥራዎቿን ለገበያ የማብቃት ትልም አላት።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG