በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የነርሶች ሞያዊ ተግዳሮቶች እና መፍትሔያቸው  


የነርሶች ሞያዊ ተግዳሮቶች እና መፍትሔያቸው  
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:02 0:00

እ.ኤ.አ. በ2020 የዓለም የጤና ድርጅት በአወጣው መረጃ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ነርስ ለአንድ ሺሕ ሰው እንኳን አይደርሰውም፡፡ አገሪቱ፣ እየጨመረ ካለው አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥሯ አኳያ፣ ነርሶችን በብዛት ማሠልጠን እንደሚያስፈልጋት አኀዛዊ መረጃው ያመላክታል፡፡

የሐኪሞች ቡድን አካል ኾነው የሚሠሩት ነርሶች፣ ታካሚዎች በአገባቡ ማገገም እንዲችሉ የመከባከብ ሚና አላቸው፡፡ ከሕሙማን ጋራ በሚኖራቸው መስተጋብር፣ የሚጠይቀው ሥነ ምግባር እና በስሜት ላይ የሚያሳድረው ጫና፣ “ለሞያው መሰጠትን ይሻል፤” የምትለው፣ ዳግማዊት አየለ/ሲስተር/ ናት፡፡

ዳግማዊት፣ ከ10 ዓመት በላይ በሞያው ላይ መቆየቷንና በላንድማርክ ሆስፒታል ሜትረን ነርስ(የነርሶች ሓላፊ) ኾና በመሥራት ላይ ትገኛለች፡፡ ከቪኦኤ ጋቢና ጋራ በነበራት ቆይታ፣ ወደ ሞያው የሚገቡ ነርሶች ሊዘጋጁባቸው እና ራሳቸውን ጠብቀው ስኬታማ ለመኾን ስለሚችሉባቸው መንገዶች ተሞክሮዋን አካፍላናለች፡፡

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያግኙ/

XS
SM
MD
LG