በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስጦታቸውን እንስጣቸው 


ስጦታቸውን እንስጣቸው 
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:57 0:00

እምነቴ ድል ነሳ፣ "ስጦታቸውን እንስጣቸው" የተሰኘ፣ በጡት ማጥባት ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ደራሲ ናት። እምነቴ፣ ከጊዜው ቀድሞ የተወለደ ልጇ፣ መሠረታዊ የእድገት መመዘኛዎችን እንዲያሟላ ለማድረግ መፍትሔ በምትሻበት ወቅት ያገኘችው ምላሽ፣ የጡት ወተትን በደንብ ማጥባት የሚለው ነበር።

ይኹን እንጂ፣ ጡት ማጥባት፥ እውቀትንና ጥንቃቄን የሚሻ እንደኾነም መማሯንም ትገልጻለች። የትምህርቷን ውጤታማነት ለማረጋገጥም፣ ዕለት ዕለት ማስታወሻ ትወስድ እንደነበር ትገልጻለች።

ቆይታ፣ በልጇ ላይ ለውጥን ያየችው እምነቴ፣ ይህን እውቀቷንና ግንዛቤዋን በመጽሐፍ አሳትማለች። ባለፉት ዓመታት፣ በተለያዩ የሕክምና ጣቢያዎች ውስጥ፣ ስለ ጡት ማጥባት፣ በበጎ ፈቃድ ለእናቶች ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ አጫጭር ሥልጠናዎችን ስትሰጥ መቆየቷን ትናገራለች።

በተጨማሪም፣ በሥነ ምግባር እና በታሪክ ላይ የሚያተኩሩ ሌሎች ሁለት መጻሕፍትንም ለኅትመት ብርሃን አብቅታለች።

XS
SM
MD
LG