በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካዊ ጭንብሎች እና የኮሚክ መጽሐፍ የተካተቱበት ትዕይንት 


አፍሪካዊ ጭንብሎች እና የኮሚክ መጽሐፍ የተካተቱበት ትዕይንት 
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:27 0:00

ባሳለፍነው ቅዳሜ፣ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በዐዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል፣ አፍሮ ማስክስ የተሰኘ ዲጂታል ጥበብንና የአፍሪካውያንን የ“ጭንብል” ባህል ያጣመረ ትዕይንት ተከፍቷል፡፡ በተመሳሳይ፣ በዕለቱ ‘ቡግናድ’ የተሰኘ ተከታታይ የኮሚክ መጽሐፍ የመጀምሪያ ክፍልም ተመርቋል፡፡

አፍሮ ፊውቸሪዝም በተሰኘው፣ አፍሪካዊ ማንነትን ከሥልጣኔና ከቴክኖሎጂ ጋራ በማዋሐድ የሚሠሩ ፊልሞችንና የፈጠራ ሥራዎችን የሚሠራው ዲጂታል ጥበብ ባለሞያው ፋኑኤል ልዑል፣ በቀጣይ፣ እነዚኽን ሥራዎች ወደ ሕይወት ማምጣት እና አፍሪካዊ ልዕለ ኀያላን ያሉበት የፊልም ሥራ ለመሥራት ሐሳብ እንዳለው፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡

ኤደን ገረመው፣ በመጽሐፉ እና በዐውደ ትዕይንቱ ዙሪያ፣ ከፋኑኤል ጋራ ቆይታ አድርጋ ዘገባ አሰናድታለች፡፡

XS
SM
MD
LG