በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲጂታል የነዳጅ መተግበሪያው ይዘት እና ጥያቄዎቹ 


ዲጂታል የነዳጅ መተግበሪያው ይዘት እና ጥያቄዎቹ 
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:54 0:00

ከሳምንታት በፊት ዐዲስ አበባ ላይ የተጀመረውና ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ገቢራዊ የኾነው፣ የነዳጅ ዘይት ዲጅታል ግብይት፥ በነዳጅ ማደያዎች ረዥም ሰልፍ እንዲኖር ማድረጉን፣ እንዲሁም ደግሞ በቂ ግንዛቤ ሳይፈጠር ሙሉ በሙሉ እንዲሠራበት በመወሰኑ አንዳንዶች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ከጥሬ ገንዘብ ንክኪ ውጭ የኾነው ዲጅታል የነዳጅ ግብይት፣ በኢግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አማካይነት ወደ ሥራ ገብቷል። የኢግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ፣ ከዚኽ ቀደም፥ “ጉዞ ጎ”፣ “ካሽ ጎ”፣ እንዲሁም “ዱቤ አለ” የሚሉ መተግበሪያዎችን ወደ ሥራ በማስገባት ይታወቃል።

የነዳጅ መተግበሪያውን ይዘት፣ እንዲሁም ከመተግበሪያው ጋራ በተያያዘ ስለሚነሡ ቅሬታዎች፣ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በርሱፈቃድ ጌታቸው አነጋግረን ያሰናዳነው ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል፡፡

XS
SM
MD
LG