በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አደጋ የደቀነው የሕፃናት ስክሪን አጠቃቀም  


አደጋ የደቀነው የሕፃናት ስክሪን አጠቃቀም  
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:04 0:00
ለሕፃናት አካላዊ እና ሥነ ልቡናዊ እድገት እጅግ አስፈላጊ ከኾኑ ነገሮች አንዱ፣ ዕድሜያቸውን ያማከለ ጨዋታ ነው። ከዘመናዊነት እና የሕዝብ ቁጥር መጨመር ጋራ ተያይዘው በመጡ የአኗኗር ዘይቤዎች ምክንያት፣ በዓለም ላይ የሕፃናት የጨዋታ ሰዓት መቀነሱን ባለሞያዎች ይናገራሉ።
በዩናይትድ ስቴትስ የተደረገ አንድ ጥናት፣ ባለፉት 16 ዓመታት፣ የሕፃናት የጨዋታ ሰዓት፣ 30 በመቶ እንደቀነሰ ጠቁሟል። ለዚኽም እንደ ምክንያት የተጠቀሱት፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ከአደጋ ለመከላከል በሚል ከእንቅስቃሴ በማቀባቸው፣ በቂ የመጫወቻ ሥፍራ አለመኖር፣ የወላጆች በተለያዩ ጉዳዮች መጠመድ እና ቴክኖሎጂ እንደኾኑ ጥናቱ ያስረዳል።
ጥቂት የማይባሉ ወላጆች፣ ልጆቻቸው እንዳይረብሹ በማለት፣ ቴሌቪዥን መመልከትን ለረጅም ሰዓት ይፈቅዳሉ፤ ሞባይል ስልኮችንና አይፓዶችን ይሰጣሉ። ይኹን እንጂ፣ የልጆች የስክሪን ሰዓት ገድብ ካልተበጀለት፥ የትኩረት ማጣት፣ የንግግር ክህሎት እና የዐይን እይታ ድክመት፣ የሰውነት ክብደት አለቅጥ መጨመር አሊያም ደግሞ ምግብ በአግባቡ አለመመገብ እና ሌሎችም የአካላዊ እድገት ተጽእኖዎች እንዳሉት፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አጠቃላይ ሐኪም እና የሕፃናት የኹለንተናዊ እድገት ባለሞያ ዶር. ቱሚም ጌታቸው ይናገራሉ።
XS
SM
MD
LG