በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዐዲሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አወቃቀር በመቃወማቸው መታሰራቸውን ነዋሪዎች ገለፁ


ዐዲሱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አወቃቀር በመቃወማቸው መታሰራቸውን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:00 0:00

ዐዲሱን፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አወቃቀር በመቃወማቸው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአርባ ምንጭ ከተማ እና የጋሞ ዞን ነዋሪዎች እንደታሰሩ፣ የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ።

የፓርቲው አመራሮች፣ ዛሬ ረቡዕ፣ በሐዋሳ ከተማ በሰጡት መግለጫ፣ በዐዲሱ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሥራ አስፈጻሚ ቢሮዎች ድልድል፣ በጋሞ ሕዝብ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ እንዳልኾነ ተናግረዋል።

የጋሞ ዞን አስተዳደር የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች መምሪያ ሓላፊ ዔደን ንጉሤ፣ በከተማው ሁከት ለመፍጠር ሲሞክሩ ታስረው ከተለቀቁት ውጪ፣ የክልሉን አደረጃጀት በመቃወማቸው የታሰሩ ሰዎች እንደሌሉ በመግለጽ አስተባብለዋል። ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG