በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዛሬ የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ በዓል ነው - የአርበኞች ቀን!


ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ አርሊንግተን ቨርጂንያ ውስጥ በሚገኘው ብሔራዊ መካነ መቃብር አበባ የማኖር ሥነ ስርዓት
ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ አርሊንግተን ቨርጂንያ ውስጥ በሚገኘው ብሔራዊ መካነ መቃብር አበባ የማኖር ሥነ ስርዓት

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ አርሊንግተን ቨርጂንያ ውስጥ በሚገኘው ብሔራዊ መካነ መቃብር በመሄድ ለሀገሪቱ 22ሚሊዮን አርበኞች ያላቸውን ክብር ይገልፃሉ።

ኦባማ በተጨማሪም “ያልታወቁ ወታደሮች” አፅም በአረፈበት መካነ መቃብር ላይ በሚከናወነው የአንድ ሰዓት የአበባ የማኖር ሥነ ስርዓት ላይም እንደሚካፈሉ ታውቋል።

“ያልታወቁ ወታደሮች መካነ መቃብር” የሚባለው ሕይወታችውን ለሀገሪቱ የሰጡ በቁጥር የማይገለፁና የማይታወቁ የጦር አባላት ያረፉበት ስፍራ ነው።

ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ጧት ኋይት ሀውስ ውስጥ ለአርበኞችና ቤተሰቦቻቸው የቁርስ ግብዣ አድርገዋል።

XS
SM
MD
LG